ወርኃ ሰኔ

፶፬ ወረደ እግዚእነ

ለእመ ኮነ በዓለ ሚካኤል በሰንበት አመ ፲ወ፪ ለሰኔ መዝሙር ወረደ እግዚእነ

፶፬.፩ (በ፭/ን) ወረደ እግዚእነ ውስተ ሲኦል ወይቤሎሙ ለእለ ውስተ ደይን በእንቲአክሙ ተሰቀልኩ ዲበ ዕፅ ወተረግዘ ገቦየ በኲናት አንትሙኒ በዝኒ ኢነሳሕክሙ በእንቲአክሙ ተቀነዋ እደውየ ወእገርየ ወተጸፍዐ መልታሕቴየ (አ) በእንቲአክሙ አስተዩኒ ብሂዐ ከርቤ ቱሱሐ ዘምስለ ሐሞት በቅድመ ጲላጦስ ወሊቃነ ካህናት (አ) ናሁ ወሀብኩክሙ ሰንበተ ክርስቲያን ዕረፍተ ትኩንክሙ በእንተ ሚካኤል መልአከ ምክርየ ወጳውሎስ ፍቁርየ ወኵሎሙ ቅዱሳንየ አእኰትዎ ኵሎሙ እለ ውስተ ደይን ወዘንተ ብሂሎ ዐርገ ኢየሱስ ሰማያተ አብሆሙ አቡሆሙ ሀገረ ቅድስተ ኢየሩሳሌም አግዓዚተ።

ትርጕም፦

ጌታችን ወደ ሲኦል ወርዶ በቅጣት ውስጥ ለነበሩት እንዲህ አላቸው ስለ እናንተ በመስቀል ተሰቀልኩ ጐኔን በጦር ተወጋሁ እናንተ ግን በዚህ አልተጸጸታችሁም (ሕማሙ ሞቱ ሕይወታቸው ስለሆነ) ስለ እናንተ እጄን እግሬን ተቸነከርኩ ፊቴን በጥፊ ተመታሁ ስለ እናንተ በካህናት አለቆችና በጲላጦስ ፊት ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ መፃፃና ከርቤ አጠጡኝ እነሆ ስለ መልአከ ምክሬ ስለ ሚካኤል ስለ ወዳጄ ስለ ጳውሎስ ስለ ሁሉም ቅዱስን ዕረፍት ትሆናችሁ ዘንድ ሰንበተ ክርስቲያንን ሰጠኋችሁ በፍርድ ውስጥ ያሉት ሁሉ አመሰገኑት ይህንን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዐረገ አባታቸው ነፃ ወደምታወጣ ሀገራቸው ወደ ኢየሩሳሌም አገባቸው።

፶፬.፪ የዕለቱ ምንባባት፦

፩ጢሞ ፫፥፲፬ – ፍ፤

፩ጴጥ ፫፥፲፭ – ፍ፤

ግብ ፩፥፮ – ፲፪፤

ወንጌል፦ ሉቃ ፳፪፥፴፩ – ፵፯፤ 

ቅዳሴ፦ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ 

፶፬.፫ የዕለቱ ምስባክ፦ 

ሠረገላቲሁ ለእግዚአብሔር ምዕልፊተ አዕላፍ ፍሡሐን፤

እግዚአብሔር ውስቴቶን በሲና መቅደሱ፤

ዐረገ ውስተ አርያም ፄዊወከ ፄዋ። መዝ ፷፯፥፲፯፤

ትርጕም፦ 

የብዙ ብዙ ሺህ የእግዚአብሔር ሠረገላዎች ደስተኞች ናቸው፤

እግዚአብሔር በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው፤

ምርኮን ማርከህ ወደ ሰማይ ወጣህ።

ምሥጢር፦

የብዙ ብዙ የሚሆኑ የእግዚአብሔር ማደሪያ እስራኤል ከአንዲት ቀን በቀር ኃዘን አላገኛቸውም ደስ ብሏቸው ይኖራሉ እንጂ። በአካን ወልደ ከርሚ ምክንያት ኢያሱ ከታቦተ ጽዮን ፊት ተደፍቶ ሲለምን ውሏልና። አንድም የእግዚአብሔር ማደሪያ የሚሆኑ ሐዋርያት በጸጋ በክብር ደስ የተሰኙ ናቸው

ውስቴቶን ለእስራኤል ነው በእስራኤል አድሮ የሚኖር እግዚአብሔር በመመስገኛው ቦታ በጽርሐ አርያም አለ አንድም በሲና በተሠራች መቅደሱ አድሮ የሚኖር እግዚአብሔር በእስራኤል አድሮባቸው ይኖራል፤

እስራኤልን ይዘህ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣህ አንድም ነፍሳትን ይዘህ ከሲኦል ወደ ገነት ወጣህ አንድም ልዕልናህን ገለጥህ። 

ሰኔ ፲፪ በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ወአፎምያ ወላሊበላ ንጉሥ 

ዘነግህ ምስባክ፦ 

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ፤ 

ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ፤ 

ጠዓሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር። 

ወንጌል፦ ማቴ ፳፬፥፴ ߺ ፴፮፤ 

ዘቅዳሴ ምንባብ፦ 

ኤፌ ፩፥፲፫ ߺ ፍጻሜ፤

ይሁዳ ፩፥፱ ߺ ፲፬፤

ግብ ፩፥፲ ߺ ፲፪፤

ወንጌል፦ ማቴ ፳፭፥፲፬ ߺ ፴፩፤ 

ቅዳሴ፦ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ 

ዘቅዳሴ ምስባክ፦ 

ሶበ ትሬእዮሙ ለጠቢባን ይመውቱ፤ 

ወከማሁ ይትኀጐሉ አብዳን እለ አልቦሙ ልብ፤

ወየኀድጉ ለባዕድ ብዕሎሙ። መዝ ፵፰፥፲፤ 

ትርጒም፦ 

ጠቢባን ሲሞቱ ባየሃቸው ጊዜ፤ 

እንደዚሁ ልብ የሌላቸው ሰነፎች ይጠፋሉ፤ 

ገንዘባቸውንም ለሌላ ይተዋሉ። 

ምሥጢር፦ 

ባለጠጎች ሲሞቱ ባየህ ጊዜ አታድንቅ፤ ጠቢባን አላቸው አንዱን ሁለት፣ ሁለቱን ሦስት፣ ሦስቱን ሁለት ያደርጋሉና፤ ቦ ጠቢባን ጻድቃን ሲሞቱ ባየህ ጊዜ ዕፁብ ዕፁብ አትበል ሞቶሙሰ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ውእቱ የጻድቃን ሞታቸው ሕይወታቸው ነው እንዲል፤ 

አእምሮ የሌላቸው ኃጥአን ይሞታሉ፤ ቦ አእምሮ የሌላቸው ኃጥአን ስንኳ ይሞታሉ፤ አብዳን አላቸው ለበጎ ነገር ሰነፎች ናቸውና፤ ቦ ኃጥአን በሥጋ ሲሞቱ እንዳየህ በነፍስም ይሞታሉ፤ ጠቢባን አላቸው ኃጥአንን ለክፉ ነገር ይራቀቃሉና፤ ለእከይሰ ጠቢባን እሙንቱ ለክፉ ነገር ጠቢባን ናቸው እንዲል፤  

ገንዘባቸውን ለባዕድ ይተዋሉ፤ ምነው ልጃቸው ይወርሰው የለምን ቢሉ የክፉን ሰው ገንዘብ ስንኳን ልጅ ባዕድ አያገኘውምና፤ ቦ ልጁን ሳይቀር ባዕድ አለው እናቱን አባቱን ቀብሮ ዋይ ዋይ እያለ ይመለሳልና፤ ከቀረው ቤተሰብ በገንዘቡ ይጣላልና፤ ቦ ከሞተ በኋላ መብት ኑሮት ለሌላ የሚሰጥ ሆኖ አይደለም እግዚአብሔር ለወደደው የሚሰጠው ስለሆነ ነው እንጂ፤  

፶፭ አባ ገሪማ

በዓለ አባ ገሪማ ለእመ ኮነ በሰንበት መዝሙር (ሰኔ ፲፯)

፶፭.፩ (በ፫/ሙ) አባ ገሪማ ጸሎትከ ትባርከኒ አባ ገሪማ ጸሎትከ ትባርከኒ ትክበር ነፍስየ በቅድሜከ ዮም (አ) አባ ገሪማ በጸሎቱ ነግሀ ይዘርዕ ኪነቶ ወሠርከ የአርር ገራህቶ (አ) ወሠርከ የአርር ገራህቶ ወበዕለቱ አዕተወ ዐውዶ (አ) ወበዕለቱ አዕተወ ዐውዶ ከመ መላእክት ይመስል ሕይወቱ (አ) ከመ መላእክት ይመስል ሕይወቱ ወይትዐፀፍ አልባሰ መንግሥቱ አባ ገሪማ ጸሎትከ ትባርከኒ ገሪማ ገረምከኒ አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና።

ትርጕም፦

አባ ገሪማ ጸሎትህ ትባርከኝ ዛሬ ነፍሴ በፊትህ ትክበር አባ ገሪማ በጸሎቱ ጠዋት ዘርቶ ማታ መከሩን ይሰበስባል በዕለቱ ወደበአቱ አስገባ ሕይወቱ የመላእክትን ይመስላል የመንግሥት ልብሱን ይጎናጸፋል አባ ገሪማ ጸሎትህ ትባርከኝ ገሪማ አስደነቅኸኝ አስኬማህ/ምንኩስናህ ምንም ጥፋት/ነውር የለባትም።

፶፭.፪ የዕለቱ ምንባባት፦

፪ቆሮ ፱፥፩ – ፍ፤

፩ጴጥ ፪፥፩ – ፲፫፤

ግብ ፬፥፴፩ – ፍ፤

ወንጌል፦ ማር ፪፥፲፬ – ፍ ወይም ሉቃ፮፥፳ – ፍ

ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት (፫፻) – ግሩም

፶፭.፫ የዕለቱ ምስባክ፦

እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ፤

ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል፤

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን። መዝ ፹፫፥፮;

ትርጉም፦

የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና፤

ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል፤

የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።

ምሥጢር፦

ዘሩባቤል መምህረ ሕግ ነውና በረከትን ይሰጣል።አንድም መምህረ ሕግ ዘሩባቤል በረከትን ይሰጣል ይሰጣልና ከኃይል ወደኃይል ይሄዳል ይሄዳልና የካህናት ፈጣሪ በሰባ ዘመን ሚጠተ ሥጋውን በማድረግ ይገለጣል።

አንድም ሊቀ ጳጳሳት መምህረ ሕግ ነውና በረከትን ይሰጣል አንድም መምህረ ሕግ ሊቀ ጳጳሳት በረከትን ይሰጣል ይሰጣልና ከእውቀት ወደእውቀት ይሄዳል ይሄዳልና። የካህናት ፈጣሪ በአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በማኅፀነ ማርያም በልብሰተ ሥጋ ይገለጣል።

፶፮ ናክብር ሰንበቶ

መዝሙር ናክብር ሰንበቶ ከሰኔ ፲፰ እስከ ሰኔ ፳፬

፶፮.፩ (በ፩/ዝ) ናክብር ሰንበቶ በጽድቅ ወኢንኅድግ ሥርዓቶ ለዘውእቱ ባሕቲቱ ሃሌ ሉያ ጻድቅ ውእቱ ጽድቀ ይኴንን በመንግሥቱ ሃሌ ሉያ ይገብር ነግሀ እንተ ጸብሐት የሀበነ ምሕረቶ ወንሕነኒ ርቱዐ ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ አምላክነሰ አምላከ አድኅኖ ይክል ኵሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጽድቅ ቃሉ ወእሙን ነገሩ።

ትርጕም፦

ሰንበትን በእውነት እናክብር ሥርዓቱን አንተው ብቻውን ላለ ለእሱ ምስጋና ይገባል ሃሌ ሉያ ጻድቅ ነውና በመንግሥቱ እውነትን ይፈርዳል ሃሌ ሉያ ሌሊቱን ማለዳ ያደርጋል በየማለዳው ይቅርታውን ይሰጠናል እኛም እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባል ሃሌ ሉያ አምላካችን የማዳን አምላክ ነው ሁሉን ይችላል የሚሳነው የለም ሃሌ ሉያ ቃሉ እውነት ነው ነገሩም የታመነ ነው።

፶፮.፪ የዕለቱ ምንባባት፦

ሮሜ ፭፥፲፪ – ፍ፤

፫ዮሐ ፩፥፩ – ፍ፤

ግብ ፲፮፥፩ – ፲፬፤ 

ወንጌል፦ ማቴ ፳፪፥፩ -፳፫

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ

፶፮.፫ የዕለቱ ምስባክ፦

አንተሰ እግዚኦ መሐሪ ወመስተሣህል፤

ርኁቀ መዓት ወብዙኀ ምሕረት ወጻድቅ፤

ነጽር ላዕሌየ ወተሣሃለኒ። መዝ ፹፭፥፲፭

ትርጕም፦

አቤቱ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ፤

መዓትህ የራቀ ምሕረትህም የበዛ እውነተኛ ነህ፤

ወደእኔ ተመልከት ይቅርም በለኝ።

ምሥጢር፦

አቤቱ አንተ ግን ቸር ይቅር ባይ ነህ ይቅር ባይ ነህ እኮ ይቅር ባይ ነህና፤

መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የቀረበ አንድም መዓትህ ያነሰ ምሕረትህ የበዛ የባሕርይ አምላክ ነህ፤

ኪያየ ሲል ነው እኔን በዐይነ ምሕረት ዐይተህ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ።  

ሰኔ ፳፩ በዓለ እግዝእትነ ማርያም 

ዘነግህ ምስባክ፦ 

ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ፤ 

ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ፤ 

አንተ ወታቦተ መቅደስከ። መዝ ፻፴፩፥፯፤

ትርጒም፦ 

የጌታችን እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንሰግዳለን፤ 

አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ 

አንተና የመቅደስህ ታቦት። 

ምሥጢር፦ 

የጌታችን እግር በቆመበት በቤተ መቅደስ እንሰግዳለን፤ እግዚአብሔር በቆመበት መልአክ፣ መልአክ በቆመበት እግዚአብሔር አይለይምና ቤተ መቅደስ የተሠራ ከዚያ ነው ዳዊት የቤተ መቅደስን ነገር ሲሻ ግብር ቢገባ የበለጠ የሥጋዌ ነገር ተገልጾለታል ጥቂት ሲሹ ብዙ መግለጥ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና፤ ቦ የጌታችን እግር በቆመበት በቀራንዮ እንሰግዳለን፤ ሠለስቱ ምዕት ሰው ሁሉ በዓመት በዓመት ቀራንዮ እየሄደ እጅ ይንሣ ብለዋል ይህስ ለሁሉ አይቻልም ብሎ ሥጋ ወደሙ የተሠዋበት ሁሉ ቀራንዮ ይባላልና ከዚያ እጅ ይንሣ ብለዋል፤ 

አቤቱ ዕረፍተ ትፍሥሕት ወዳለበት ወደኢየሩሳሌም ተነሥ፤ ቦ ትሩፋንን ወደምታሳርፍበት ወደኢየሩሳሌም ቦ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደመንግሥተ ሰማያት ምእመናንን ይዘህ ተነሥ፤ 

አንተና የማደሪያህ ጌጥ የሚሆኑ ነቢያት ካህናትን ቦ ታቦተ ጽዮንን ቦ እመቤታችንን ቦ ምእመናንን ይዘህ ተነሥ። 

ወንጌል፦ ሉቃ ፩፥፴፱ – ፶፯፤

ዘቅዳሴ ምንባብ፦ 

ኤፌ ፪፥፲፫ – ፍጻሜ፤

፩ጴጥ ፪፥፬ – ፲፩፤

ግብ ፩፥፲፪ – ፲፭፤

ወንጌል፦ ማቴ ፲፮፥፲፫ – ፳፤ 

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ 

ዘቅዳሴ ምስባክ፦ 

ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፤ 

እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሐወክ፤ 

ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ። መዝ ፵፭፥፬፤

ትርጒም፦ 

ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ፤ 

እንዳትታወክም እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤

እግዚአብሔር ፊት ለፊት ይረዳታል፤ 

ምሥጢር፦ 

ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያው ኢየሩሳሌምን አቀናት አጸናት፤ 

መከራ መጥቶባት እንዳታዝን እንዳትጨነቅ ሀገሪቱ እንዳትፈታ እግዚአብሔር በረድኤት አድሮባት ይኖራል፤ 

በመከራዋ ጊዜ ፊታውራሪ ሆኖ ይረዳታል፤ 

ቦ ልዑል እግዚአብሔር ማደሪያው እመቤታችንን አነጻት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ አጸናት እንድትችለው አደረጋት፤ 

መከራ መጥቶባት እንዳታዝን እንዳትጨነቅ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ አድሮ ይኖራል፤ ቦ በዘመዶቿ ፍዳ እንዳትያዝ በማኅፀኗ አድሮ ይኖራል፤ 

በአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን መከራዋ ጊዜ በኵር ሆኖ ይረዳታል ይጠብቃታል።  

፶፯ ሠርዐ ሰንበተ

አመ ፳ወ፭ ለሰኔ በአተ ክረምት መዝሙር ሠርዐ ሰንበተ 

፶፯.፩ (በ፭/ሴ) ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ለእለ በሰማይ ወለእለ በምድር ለእለ በባሕር ወለእለ በየብስ (ሠ) ለአበዊነ ለነቢያት ወለሐዋርያት (ሠ) ለጳጳሳት ወለቀሳውስት ለዲያቆናት ወለመነኮሳት (ሠ) ለጻድቃን ወለኃጥአን ለሙታን ወለሕያዋን ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ሰንበቱሰ ለክርስቶስ ይእቲ ወማኅደረ ስሙ ለልዑል።

ትርጕም፦

ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ፤ በሰማይናበምድር በባሕርና በየብስ ላሉት ሁሉ። ለአባቶቻችን ለነቢያትና ለሐዋርያት፤ ለጳጳሳትና ለቀሳውስት ለዲያቆናትና ለመነኮሳት፤ ለጻድቃንና ለኃጥአን ለሙታንና ለሕያዋን፤ ለሰው ዕረፍት ትሆን ዘንድ ሰንበትን ሠራ ይህች የክርስቶስ ሰንበት ናት የልዑል የስሙ መጠሪያም ናት።

፶፯.፪ የዕለቱ ምንባባት፦

፪ቆሮ ፲፡፩ – ፍጻሜ፤ 

፩ጴጥ ፭፡፩ – ፍጻሜ፤ 

ግብ ፳፡፳፰ – ፍጻሜ፤ 

ወንጌል፦ ማቴ ፲፮፡፩ – ፲፫፤ 

ቅዳሴ፦ ዘሐዋርያት 

፶፯.፫ የዕለቱ ምስባክ፦ 

ወአንተ ገበርከ አድባረ ምድር ኵሎ፤ 

ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ፤ 

ወተዘከር ዘንተ ተግባረከ። መዝ ፸፫፥፲፯፤

ትርጒም፦ 

አንተ የምድር ዳርቻዎችን ሁሉ ሠራህ፤ 

በጋና ክረምትን አንተ አደረግህ፤ 

ይህን ፍጥረትህን አስብ። 

ምሥጢር፦ 

(አድባረ) ተራራውን ኮረብታውን

(ወምድረ) ደልዳላውን መሬት የፈጠርህ አንተ ነህ።

ዘጠኝ ወር በጋን ሦስት ወር ክረምትን የፈጠርህ (የሠራህ) አንተ ነህ

ይህን ያደረግህለትህን ፍጥረትህን አስብ አስበህ አውጣን።  

ቦ አድባረ ወምድረ – ሙሴ አሮንን ሰባ ሊቃናትን ያስነሣህ አንተ ነህ፤

ክረምተ ወሐጋየ – ዘመነ ኤልያስን ያመጣህ አንተ ነህ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ድርቅ ሆኗልና።

ቦ አድባረ ወምድረ – ልዑላኑን ትሑታኑን የፈጠርህ አንተ ነህ።

ክረምተ ወሐጋየ፦ ተማርከው ሲሄዱ የሚጠጡት አጥተው ማድጋቸውን እያንኳኩ ወርደዋል በሚጠት ጊዜ ዝናም እየዘነመላቸው በየወንዙ ውኃ ሞልቶላቸው እየጠጡ ወጥተዋልና።

ቦ አድባረ ወምድረ – ሐዋርያትን ሰባ አርድእትን ያስነሣህ አንተ ነህ።

ክረምተ ወሐጋየ – ኦሪትን ወንጌልን የሠራህ። በክረምት ቅጠል እንጂ ፍሬ እንዳይገኝ በኦሪትም ተስፋ እንጂ ሀብት ሥርየት አልተሰጠምና። በበጋ ፍሬ እንዲገኝ በወንጌል ሀብት ሥርየት ተገኝቷልና።

፶፰ ደምፀ እገሪሁ

መዝሙር ደምፀ እገሪሁ ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፪

፶፰.፩ (በ፪/ኒ) ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን (ደ) ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን (ደ) ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም።

ትርጕም፦

የዝናም እግሩ ተሰማ ዝናም በሚዘንም ጊዜ ነዳያን ደስ ይሰኛሉ ዝናም በሚዘንም ጊዜ የተራቡ ይጠግባሉ ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ የዝናም እግሩ ተሰማ።

፶፰.፪ የዕለቱ ምንባባት፦

፩ቆሮ ፲፭፥፴፫ – ፶፩፤

ያዕ ፭፥፲፮ – ፍ፤

ግብ ፳፯፥፲፩ – ፳፩፤ 

ወንጌል፦ ሉቃ ፰፥፩ – ፳፪

ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ

፶፰.፫ የዕለቱ ምስባክ፦

ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና፤

ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር፤

ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር። መዝ ፻፵፮፥፰

ትርጕም፦

ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፤

ለምድር ክረምትን የሚያዘጋጅ፤

በተራሮች ላይ ሣርን የሚያበቅል እግዚአብሔር ነው።

ሰኔ ፳፱ ተዝካረ ልደቱ ለእግዚእነ 

ዘነግህ ምስባክ፦ 

ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል፤ 

በብርሃኖሙ ለቅዱሳን፤ 

ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ። 

ወንጌል፦ ማቴ ፪፥፩ ፲፫፤ 

ዘቅዳሴ ምንባብ፦ 

፩ጢሞ ፫፥፲፫ – ፍጻሜ፤

፩ዮሐ ፬፥፱ – ፲፰፤

ግብ ፱፥፳ – ፳፫፤

ወንጌል፦ ማቴ ፲፮፥፳፬ – ፍጻሜ፤ 

ቅዳሴ፦ ዘባስልዮስ 

ዘቅዳሴ ምስባክ፦ 

ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና፤ 

ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር፤ 

ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር።