የሀ ነጠላ ግስ

ሀልሀ (ቀተ/ባረ) – ወደረ

ላሕልሐ (ማህ) – ራሰ

ለሕሐ (ክህ) – ቀዳ

ለምሐ (ቀተ) – ለማ

ለስሐ (ቀተ)- አልጫ ሆነ

ለብሐ (ቀተ) – ሠራ

ለትሐ (ቀተ) – ተጎነጨ

ሎሐ (ቀተ) – ጻፈ

ለጥሐ (ቀደ) – ገበረ

ማሕምሐ (ማህ) – ፈረሰ አፈረሰ

መልኀ (ቀተ) – መዘዘ

መልሐ (ቀደ) – አጣፈጠ

መስሐ (ቀተ) – ምሳ አደረገ

መርሐ (ቀተ) – መራ

መትሐ (ቀተ) – ሳሳ ቀጠነ

መንዝሐ (ተን) – ተደላደለ ተቀማጠለ

መድሐ (ቀተ) – ፈጨ

ሞርቅሐ (ጦመ) – ላጠ

ሞቅሐ (ጦመ) – አሰረ

ሞጥሐ (ጦመ) – ለበሰ

ሞጽሐ (ጦመ) – ጠመቀ

ሳሕስሐ (ማህ) – አፈገፈገ

ሰርሐ (ቀተ) – ሠራ ደከመ

ሠርሐ (ቀደ) – አቅናና አከናወነ አሰናበተ

ሣርኀ (ባረ) – አበራ

ሰብሐ (ቀደ) – አመሰገነ

ሠብሐ (ቀተ) – ሰባ

ሰንሐ (ቀተ) – በራ ሆነ

ሰይሐ (ቀደ) – ታመመ

ሴሐ (ቀተ) – ወቀጠ

ሰጥሐ (ቀተ) – አሰጣ

ሰፍሐ (ቀተ) – ዘረጋ

ረምሐ (ቀተ) – ወጋ

ረስሐ  (ቀተ)  – ጐሰቈለ፤ በደለ፤

ረቅሐ (ቀተ) – ጋረጠ (የጋሬጣ)

ረብሐ  (ቀተ)   –   ረባ፤ በዛ፤ ጠቀመ፤

ረውሐ    (ቀደ)   –  ቀደደ፤ (ለልብስ)

ሮሐ (ቀተ)    –   ወለወለ፤ አራገበ፤

ረግሐ (ቀተ) – ቀደደ፣ በሳ፣ ረገጠ፤

ቃሕቅሐ (ተን) – ተቆራቆሰ፤ አሰምቶ ተናገረ፤

ቆልሐ (ቀደ) – ፍሬ ያዘ፤

ቀምሐ (ቀተ)  – አፈራ፤

ቀርሐ (ቀደ)    –  ጨለጠ፤

ቃርሐ (ባረ)     – ተኮሰ፤

ቄቅሐ (ቀተ / ሴሰ)   –  ፈተገ፤

ቄሐ (ቀተ)   –   ቀላ፤

ቀድሐ (ቀተ)     –   ቀዳ፤ በሳ፤

ባኅብኀ (ማህ) – ከረፋ፤ ቀረና፤

በኊበኈ (ተን)  – ሸተተ፤

በልኀ (ቀተ)  –  ስለት ሆነ፤

ባልሐ (ባረ) – አዳነ፤

በርሀ (ቀተ)   – በራ፤

በዝኀ (ቀተ)  – በዛ፤

በጥሐ (ቀተ) – በጣ፤

በጽሐ (ቀተ) – ደረሰ፤

ታሕትሐ (ማህ)  – ፈላ፤

ተመክሐ (ቀደ) – ተመካ

ቶስሐ (ጦመ)  – ጨመረ

ተራኅርኀ (ማህ)  –  ቸር ሆነ

ተቃድሐ (ቀተ) /ለድንበር መካለል/ – ተደነባበረ፤

ተበውሐ (ቀደ)  – ሠለጠነ፤

ተበጽሐ (ቀተ) –  ተባበረ፤

ተንሀ (ቀደ) – አገመ፤

ተዋፅኀ (ቀተ)  – ተፈጨ ተቈላ፤

ተዋህውሀ (ማህ) – ተመላለሰ፤

ተየውሀ (ቀደ) – የዋህ ሆነ፤

ቴሀ (ቀተ)  – ቀላወጠ፤

ተጋህግሀ (ማህ) – ክፍት ክፍት አለ፤

ተጋውሐ (ቀተ) – ጎረቤት ሆነ፤

ተግሀ (ቀተ) – ተጋ፤

ተጻብሐ (ቀተ)  – እንዴት አደርህ ተባባለ፤

ተፈሥሐ (ቀደ) –  ደስ ተሰኘ

ናሕንሐ (ማህ)   –   ትርፍርፍ አለ፤

ነስሐ (ቀደ)  – ተጸጸተ፤

ነስኀ (ቀተ) – ሸተተ፤ ከረፋ፤

ነቅሀ (ቀተ) – ነቃ፤

ነብሐ (ቀተ) – ጮኸ፤

ኖኀ (ቀተ) – ረዘመ፤

ነዝኀ (ቀተ) – ረጨ፤

ነድሐ (ቀተ) – ነዳ፤

ነግሀ (ቀተ) – ነጋ፤

ነጽሐ (ቀተ) – ንጹሕ ሆነ፤

ነፍኀ (ቀተ) – ነፋ፤

አምኀ (ቀደ) –  እጅ ነሣ፤

አመልትሐ (ተን) – አመሳቀለ፤

አመርግሐ (ተን) – አንከባለለ፤

አመድቅሐ (ተን) – ሠራ፤

አመብኵሐ (ተን) – አናፋ፤

አስተማዝሐ (ተን) – አቀበጠ፤

አርሳሕስሐ (ማህ) – አረሳሳ፤

አቅየሐይሐ (ማህ)  – አቅላላ፤

አብሐ (ቀተ) – አሰናበተ፤

አንሳሕስሐ (ማህ) – አነሣሣ፤

አንቆቅሐ (ጦመ) –  እንቁላል ጣለ፤

አንባሕብሐ (ማህ) – ዱብ ዱብ አደረገ፤

አንካሕክሐ (ማህ) – ፈተፈተ፤

አንግሀ (ቀተ) – ማለደ፤

አውጽሐ (ቀተ) –  አቀረበ፤

አይኀ (ቀተ) – ወረደ፤

አጸንሕሐ (ተን) – አሻተተ፤

አጽናሕንሐ (ተን) – ወዘወዘ፤