ግስ

Published by

on

ግስ የሚለውን ቃል ለመረዳት፦ ፩ ገሰ ወይም ገሰሰ – ዳሰሰ፤ ዳበሰ፤ በእጁ ነካ፤ አረጋገጠ ማለት ነው። ገሲስ ገሲሶት ንዜንወክሙ በእንተ ውእቱ ዘሀሎ እምቅድም ዘሰማዕናሁ በእዘኒነ ወዘርኢናሁ በአዕይንቲነ ወዘጠየቅናሁ “ወዘገሰሳሁ እደዊነ” – ከመጀመሪያ ስለነበረው፣ በጆሯችን ስለሰማነው፣ በዐይናችን ስላየነው፣ ስለተረዳነው፣ “በእጆቻችን ስለዳሰስነው” እንነግራችኋለን ፩ዮሐ ፩፥፩ 

ማስረጃ ጥቅሶች፦  

ኢትግስሱ መሢሐንየ – የቀባኋቸውን አትዳሱ/አትንኩ መዝ ፻፬፥፲፭

“ርእዩ እደውየ ወእገርየ ከመ አነ ውእቱ ወግሥሡኒ ወአእምሩ – እጄንና እግሬን እዩ ዳሱኝም እኔ እንደሆንሁም እወቁ” ሉቃ ፳፬፥፴፱

ከላይ ያየነውን መነሻ አድርገን ግስ ማለት፦

፦ ግስ መግሰስ፣ አንዱን ቃል ማርባት፣ ማብዛት፣ የሩቁን ለቅርብ፣ የወንዱን ለሴት፣ ያንዱን ለብዙ መስጠት ማወራረስ ማለት ነው።

፦ የቋንቋ ጓዝ የዘርና የነባር እክት ወይም ስብስብ/ምእላድ ማለት ነው።

“ሰማይ ከነግሱ ምድር ከነልብሱ” እንዲሉ ከነጓዙ ለማለት።

፦ የቋንቋ መጽሐፍ፣ የዘርና የነባር መድበል፣ መዝገበ ቃል፣ ንባቡ በፊደል የታከተ የተከተተ ማለት ነው።

በሌላ አተረጓጐም፦

መፋቅ፣ መፈቅፈቅ፣ ማጥፋት የሚል ትርጒም አለው።

ፈኑ እዴከ ወግስስ – እጅህን ዘርጋ ዳሰውም (ያለውን ሁሉ አጥፋበት) ኢዮ ፩፥፲፩

በገሰ ወይም በገሰሰ የግስ አወራረድ

ገሰ፤ ገሰሰ፤ ይገስስ – ይግስስ – ይግስስ

ሣልስ ቅጽል፦ (የመጨረሻው ፊደል ሣልስ የሆነ ማለት ነው፤ ለምሳሌ፦ ሀ ግእዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሣልስ)

ገሳሲ፣ ገሳስያን፣ (ለወንድ)

ገሳሲት፣ ገሳስያት፣ (ለሴት)

ሳድስ ቅጽል ወይም ውስጠዘ (የመጨረሻው ፊደል ሳድስ የሆነ ማለት ነው፤ ለምሳሌ፦ ሀ ግእዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሣልስ፣ ሃ ራብዕ፣ ሄ ሐምስ፣ ህ ሳድስ)

ግሱስ፣ግሱሳን፣(ለወንድ)

ግስስት፣ ግሱሳት (ለሴት)

ባዕድ ቅጽል፦

መግስስ፣ መግስሳን፣ (ለወንድ)

መግስስት፣ መግስሳት (ለሴት)

መድበል ቅጽል፦

ገሰስት (ለወንድም ለሴትም)

ግሰት (ጥ) – መዳሰስ፣ አደሳሰስ፣ ዳሰሳ፣ ዳበሳ

ግሳሴ (ጥሬ ዘር)

Leave a Reply

Discover more from በመካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ኤላም የትምህርት ማዕከል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading