መዝሙር ዘዘወረደ

Published by

on

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባዑ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕፃዲሁ በስብሐት እመንዎ (እ) ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ (እ) አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት (እ) ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወዕሌቡ ፍኖተ ንጹሐ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ

ትርጉም፦

ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በረዓድ ደስ ይበላችሁ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና ጽድቁም ለልጅ ነውና እኛ ወገኖቹ ነን። በምስጋና ወደፊቱ ቅረቡ በቤተ መቅደሱ በምስጋና እመኑት። ጾምን እንጹም ባልንጀራችንን እንውደድ እርስ በእርሳችን እንፋቀር። ሰንበትን አክብሩ ጽድቅን ሥሩ ሰንበት ስለሰው ተፈጥራለችና። ምሕረትን ፍርድን እቀኛለሁ እዘምራለሁ ንጹሕ መንገድን አስተውላለሁ። ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና ጽድቁም ለልጅ ልጅ ነውና እኛ ወገኖቹ ነን ያውም የመንጋው በጎች የነአብርሃም ወገኖች ነን።

ምስባክ፦

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት
ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዓዕ እግዚአብሔር መዝ ፪፥፲፩

ትርጉም፦

ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ
በረዓድም ደስ ይበላችሁ
እግዚአብሔር እንዳይቆጣ ጥበብን አጽኗት።

ምሥጢር፦

ከላይ ወሕዝብኒ ነበቡ ከንቶ – ሕዝቡም ከንቱ ነገርን ተናገሩ ማለትም ስቅሎ ስቅሎ ብለው ተናገሩ ብሎ ነበርና እናንተ ግን በፍርሃት በረዓድ በመንቀጥቀጥ ለእግዚአብሔር ተገዙ አለ።
በመገዛታችሁም ደስ ይበላችሁ፤ ዋጋ ያለበት ነውና፤ ደስ ሳይሰኙ መገዛት ዋጋ አያሰጥምና።

አንድም (ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወበረዓድ እንዘ ትትሐሠዩ) ይላል ደስ እያላችሁ በፍርሃት በረዓድ ተገዙ።

ጽሕፈት ድጉሰትን እርሻ ቁፋሮን አጽንታሁ ያዙ። ጽፋችሁ ደጉሳችሁ አርሳችሁ ቆፍራችሁ ብሉ ብላቸው አይሆንም አሉ ብሎ እግዚአብሔር በረኃብ እንዳይቀጣችሁ።

አንድም ኢታምልክን ጠብቁ አሥሩ ቃላትን ብሠራላቸው አንጠብቅም አሉ ብሎ እግዚአብሔር እንዳይፈርድባችሁ።

አንድም ኦሪትን ወንጌልን ጠብቁ ኦሪትን ወንጌልን ብሠራላቸው አንጠብቅም አሉ ብሎ እግዚአብሔር እንዳይፈርድባችሁ።

አንድም ጥበብ ወልድን እመኑባት “ጥበብ ሐነፀት ላቲ ቤተ ወአቀመት ሰባተ አዕማደ – ጥበብ ቤትን ሠራች ሰባት ምሰሶዎንም አቆመች” እንዲል ምሳ ፱፥፩
“ጥበብ ትዌድስ ርእሳ – ጥበብ ራሷን ታመሰግናለች” ሲራ ፳፬፥፩

ልጄን በሥጋ ብሰድላቸው አላመኑበትም ብሎ እንዳይፈርድባችሁ።

የዕለቱ ወንጌል፦

ዮሐ ፫፥፲ – ፳፭

ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ

Leave a Reply

Discover more from በመካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ኤላም የትምህርት ማዕከል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading