ወዘክህልከ ግበር ዘእንበለ ሁከት – ያለመታወክ የቻልኸውን አድርግ ፊልክስዩስ ተስእሎ ፵፯

Published by

on

ከአኃው አንዱ አባ ሰርማጣን ቸልተኛ ነኝ እበላለሁ እጠጣለሁ እተኛለሁ የተረጋጋ ልብ የለኝም ምን ላድርግ? ባለው ጊዜ የሰጠው ምክር ነው።

እሱም ሦስት ነጥቦችን ነግሮታል።

፩ ተዐገሥ ውስተ በአትከ – በበአትህ ጽና

“ሑር ሕዝብየ ወባእ ቤተከ ወዕፁ ኆኅተከ ወተኀባዕ ኅዳጠ ምዕረ – ወገኔ ሆይ ሂድ ወደቤትህ ግባ ደጅህን ዝጋ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ” እንዲል ኢሳ ፳፮፥፳፤

የዚህም ምሥጢሩ “አስተጋብእ ሕዋሳቲከ – ሕዋሳትህን ሰብስበህ” ጸልይ ማለት ነው። አንድም የጸሎቱን አንቀጽ ስልቱንና ምሥጢሩን አውቀህ ጸልይ ማለት ነው።

በቅዱስ ወንጌልም የተመዘገበው በተመሳሳይ መልኩ “ባእ ቤተከ ወዕፁ ኆኅተከ ወጸሊ ኀበ አቡከ በኅቡእ የዐሥየከ ክሡተ – ወደቤትህ ግባ ደጅህን ዝጋ ወደአባትህ በሥውር ጸልይ በግልጥ ይሰጥሃል” ተብሎ ነው ማቴ ፮፥፮

፪ ወዘክህልከ ግበር ዘእንበለ ሁከት – ያለመታወክ የተቻለህን አድርግ

፫ ወዝንቱ ግብር ኅዳጥ ዘትገብሮ ከመ ግብር ብዙኅ ዘይገብሮ እንጦንዮስ በውስተ ደብሩ – በበአትህ ጸንተህ የምትሠራው ጥቂቱ ሥራ እንጦንስ በበአቱ ሆኖ እንደሚሠራው ብዙ ሥራ ነው ማለት እንደሱ ይሆንልሃል።

እስመ ዘይፈቅድ ይግበር ዘኮነ ወኢይክል ይትዔረዮ ለዘይክል ወይገብር – የታዘዘውን ሊሠራ የሚወድ ግን አልቻለው ብሎ የሚቀርበት ሰው ተችሎት የሚሠራውን ሰው ይተካከለዋልና።

የምንችለውን ማድረግ እንዴት ይገለጣል?

፩ ለትምህርተ ወንጌል/ለጉባኤ ወንጌል የምንሰጠው ክብርና ትኩረት፤

ጽድቅኬ ኢኮነ በአምጣነ ምግባረ ሥጋ – ጽድቅ በሥራ ብዛት አይደለም። 

ማርያምሰ ተልእከት በመንፈሳ ለመንፈሳውያት ዘውእቱ ሰሚዐ ቃለ እግዚእ – ማርያም በመንፈሷ መንፈሳዊነትን አገለገለች ይኸውም ቃለ እግዚአብሔር መስማት ነው።

፪ የስጦታችን ዐይነትና መጠን፤

ጽድቅኬ ኢኮነ በብዝኃ አቅርቦ – ጽድቅ ብዙ በመስጠት አይደለም

እስመ እግዚእነ በእንተ በዓልተ ክልኤ ጸሪቅ ከመ ይእቲ አብአት ፈድፋደ እምአብዕልት – ጌታችን ሁለት መሐልቅ የሰጠችውን መበለት ብዙ ከሰጡት እሷ ብዙ እንደሰጠች ተናግሯልና።

፫ ትሕትናችንን የምንገልጥበት ሁናቴ

መጽብሐዊኒ በእንተ ትሕትናሁ ጸድቀ እምፈሪሳዊ ዘበዝኀ ጾሙ ወምጽዋቱ ወጸሎቱ – ቀራጩም ስለትሕትናው ብዙ ምጽዋት፣ ጾምና ጸሎት ካለው ፈሪሳዊ ጻድቅ ሆኖ ተመልሷል።

ቴዎፍሎስ አንዱን አበ ምኔት ከሰው ተለይተህ በጽማዌ ውስጥ ሆነህ ምን አገኘህ ብሎ ቢጠይቀው፦

አነውር ርእስየ በኵሉ ጊዜ – በየጊዜው ራሴን መንቀፍን አገኘሁ ብሎታል

፬ ጥፋታችንን የምናምንበት መንገድ 

ፈያታዊኒ ዘየማን ዘለፈ ርእሶ በጊዜ ሞቱ – ፈያታዊ ዘየማን በጊዜ ሞቱ ራሱን ዘልፏል (ንሕነ ተፈደይነ በከመምግባሪነ) ብሎ

ወበእንተዝ ደለዎ ገነት – ስለዚህ ገነት ተገባው።

ይቆየን  

Leave a Reply

Discover more from በመካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ኤላም የትምህርት ማዕከል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading