ራስን መፈለግ

Published by

on

ኅሥሥ ህላዌ ርእስከ ወአስተሐይፅ በጥዩቅ ወአንተ ትኔስሕ እስመ አልቦ ዘይወስድ ኀበ ምግባረ ጽድቅ ከመ ተዘክሮ ኃጣውእ
– ስለሰው ማውራትህን ትተህ የራስህን አኗኗር መርምር ኃጢአተኛ እንደሆንህ አንድም ፈራሽ በስባሽ እንደ ሆንህ እወቅ ከዚህ ደረጃ ከደረስህ ሰውን ከመንቀፍ ራስህን ወደመንቀፍ ትመለሳለህ የራስን ኃጢአት እንደማሰብ ትሩፋት ወደመሥራት የሚያደርስ የለምና። ተግሣጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፳፫

በሕይወታችን በማይመለከተንና ምንም ትርፍ በማናገኝበት ጉዳይ እየገባን እንዲባክን ያደርግነው ጊዜ ቀላል አይደለም። የጊዜው መባከን ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽእኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ብዙ ሰው በቤቱ ውስጥ የሚኖረው በአካሉ ነው እንጅ በልቡ ሌላ ቦታ ነው። የያዘውን የሚጥለው፣ የማያገኘውን የሚፈልገው፣ ያለበትን የሚረሳው፣ መሄድ ወደሚገባው በየምክንያቱ እየቀረ መሄድ ወደማይገባው የሚሄደው፣ በማያስጨንቀው የሚጨነቀው የራሱ በሆነው ጉዳይ አይደለም። ለሱ የተደረገለትን ከማሰብና በዚያ ከማመስገን ይልቅ ሌላ ሰው ላይ ያየው ነገር እያስቀናው ደስታውን በራሱ ያጣል። አልገባውም እንጂ ሌሎችም በእሱ እየቀኑ ደስታቸውን ያጣሉ። ለዚህ ነው ሊቁ ከእንዲህ አይነቱ  ውጣ ውረድ ወጥተን የራሳችንን ኃጢአት እያሰብን የትሩፋት ሥራዎችን ወደመሥራት እንድናድግ የመከረን። ራስን መሆን ትልቅ ነገር ነው የትም ስንሄድ የምናገኘው ራሳችንን ነውና። ኅሥሥ ህላዌከ – ኑሮህን ፈልግ ማለት ይሄ ነው። እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነው እንዳለ ሐዋርያው። እዚያ ለመግባት የሚያስችል ዝግጅት አድርጌያለሁ? ብሎ ራስን መጠየቅ ለራስ ጊዜ እንዲሰጡ ያደርጋል። በኪራይ ቤት የሚኖር ሰው ለሚቀጥለው የሚሆን ክፍያ አለኝ ብሎ ካሰበ ጊዜው ሲደርስ አይጨነቅም። በተጠየቀ ጊዜ ካስቀመጠው አንሥቶ ይሰጣልና። 

One response to “ራስን መፈለግ”

  1. ግሩም Avatar
    ግሩም

    ክቡር አባቴ መጋቤ ብሉይ፡ ክብር ያድልልን እድሜን ከተሟላ ጤና ጋር ያዽልልን!
    እራሳችንን የምንፈልግበትን አቅጣጫ (መንገዱን) ማን ያሳየን? እናንተ ኑሩልን exit እንዳንወጣም አቅጣጫዎቻችን ናችሁና!

Leave a Reply to ግሩምCancel reply

Discover more from በመካነ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ኤላም የትምህርት ማዕከል

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading