Author: elam aba
-
፩ መዝሙር ዮሐንስ አኅድዐ
፩.፩ መዝሙር ዮሐንስ አኅድዐ ከመስከረም ፩ – መስከረም ፯ (በ፭/ን) ዮሐንስ አኅድዐ እምካልአኒሁ አንሐ ወክሐ እንዘ ይብል እምላዕሉ ወረደ ቃለ አብ ወተሐውከ ማየ ዮርዳኖስ እምግርማ መለኮት ወደንገጹ ኵሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር ከማሁ ኮነ በቢታንያ በቤተ ራማ በማዕዶተ ዮርዳኖስ ወሶበ ርእዮ ዮሐንስ ለኢየሱስ ከልሐ ወይቤ ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ…
-
በእንተ ጥምቀት
በእንተ ጥምቀት ወበውእቱ መዋዕል በጽሐ ዮሐንስ መጥምቅ እንዘ ይስብክ በገዳመ ይሁዳ ዘዮርዳኖስ ከመ ናዝራዊ ይሰመይ ወልድየ ብሎ ነበርና ናዝሬት በገባበት ወራት፤ ሃያ አምስቱን ዘመን አንድ ወገን አድርጎ ወበውእቱ መዋዕል አለ። በዮሐንስ አርባውን ቀን እንደ አንድ ቀን አድርጎ ወአመ ሳኒታ እንዳለ። ቦ ወተወሊዶ ብሎ ነበርና ሰው በሆነበት ወራት፤ ቦ ለዮሐንስ ሠላሳ…
-
አእምር ከመ ማዕከለ መሥገርት ተኀልፍ
አእምር ከመ ማዕከለ መሥገርት ተኀልፍ ወከመ ቀልቀል ታንሶሱ – በወጥመድና በወጥመድ መካከል እንደምታልፍ በገደልና በገደል መካከል እንደምትመላለስ እወቅ ሲራክ ፱፥፲፫ የጥቅሱ ዐቢይ መልእክት ወጥመዱ ይይዘኛል በገደሉም እወድቃለሁ ብለህ እንደምትጠነቀቅ በመንፈሳዊ ሕይወትህም ተጠንቀቀህ ኑር የሚል ነው። ልዑለ ቃል በመባል የሚታወቀው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ይህንን የሚያጠናክር ቃል ሲናገር እንዲህ አለ “ፍርሃት ወፀድፍ…
-
ድጓ ማለት
ድጓ ማለት፦ መስተጋብዕ የሚሰበስብ የሚያሰባስብ ማለት ነው፤ በተለያየ ቦታ ያሉ ሊቃውንትን አሰባስቦ በአንድነት ለምስጋና ያቆማልና። እስትጉቡዕ የተሰበሰበ ማለት ነው፤ ከተለያዩ መጽሕፍት የተውጣጣ ድርሰት ነውና። ሠርጒ ማለት ነው፤ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ሽልማት ነውና። ድግ ማለት ነው፤ ይህም በወገብ የሚታሠር ለሰውነት ብርታት የሚሆንና ድጋፍ የሚሰጥ ነውና። (የሆድ ካሳ የወገብ ምሳ እንዲሉ)…
-
ትእምርተ ንስሐ – የንስሐ ምልክት
ትእምርተ ንስሐ – የንስሐ ምልክት አንድ ተነሳሒ ንስሐ ለመግባት ዝግጅት ማድረጉ የሚታወቅበትንና በንስሐ ሕይወት ውስጥ መኖሩን የሚያሳዩ ከሚባሉት መሠረታዊ ነጥቦች የሚከተሉትን እናያለን መግቢያ ጥቅስ፦ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ስለ ንስሐና ተነሳሕያን ባስተማረበት አንቀጽ እንዲህ አለ “ለንስሐ የሚያበቃችሁን በጎ ሥራ ሥሩ” ማቴ 3፡8፤ በጎ ሥራ ብለን የምንረዳውም ሊያድነን ከሰማያት በወረደውና ከድንግል ማርያም…
-
ትእምርተ መዊዕ – የማሸነፍ ምልክት
ትእምርት ማለት ምልክት፣ አምሳል፣ አብነት፣ ዐላማ ማለት ነው፤ ተአምር የሚለውም የዚሁ አምሳያ ነው፤ ትእምርት የሚለው ከሚታይ ምልክት ጋር የተያያዘ ሲሆን ተአምር የሚለው አስደናቂ ከሆነ ድርጊት ጋር የተያያዘ ነው። “ወይከውነክሙ ሕዝቅኤል ትእምርተ ከመ ኵሉ ዘገብረ ትገብሩ – እንዳደረገው ታደርጉ ዘንድ ሕዝቅኤል ምልክት ይሆናችኋል” የሚለው ትንቢታዊ ቃል “ትእምርት” የሚለውን ምልክት ወይም አብነት…
-
በዝየ ይከውን ካህን ህየንተ ማዕሠር – ካህኑ (የካህኑ ቃል) እንደ ማሠሪያ ነው።
ኵሉ ዘይደዊ እምነ አባግዕ የዐሥርዎ ወየዐፅዉ ላዕሌሁ ውስተ ጽልመት ወይሁብዎ ካልአ ሲሳየ ወኢየኀድግዎ ያጼኑ ነፋሰ ጥዑመ ወኢያቀርብዎ ኀበ ምርዓይ ወኢያሰትይዎ እምነቅዕ ዘሀሎ በአፍኣ ወናሁኬ በዝየ ይከውን ካህን ህየንተ ማዕሠር – ከበጎች ወገን የታመመውን በግ ለይተው ከጨለማ አግብተው ያስሩታል ደጅ ይዘጉበታል ደረቅ ሣር ይሰጡታል ነፋስ ካለበት አያሰማሩትም የጠራ ውኃ የለመለመ ሣር…
-
ሃይማኖትሰ ሃይማኖተ ጽድቅ በእንተ እግዚአብሔር

ፊልክስዩስ ተስእሎ ፻፺፮ ሊቁ ይህን ኃይለ ቃል መነሻ አድርጎ እንደሚከተለው አባታዊ ምክሩንና መልእክቱን ያስተላልፍልናል። ፩. ሃይማኖትሰ ሃይማኖተ ጽድቅ በእንተ እግዚአብሔር – ሃይማኖት ማለት በአካል ሦስት በባሕርይ አንድ ብሎ ማመን ነው። ይህም ምሥጢረ ሥላሴ ብለን የምናውቀውና የምናምነው ነው። የማይከፈል አንድነት የማይጠቀለል ሦስትነት የሚነገርበት፣ አንድነት በሦስትነት ሦስትነት በአንድነት የሚነገርበት፣ ልጅነት ያልተከተለው አባትነት፣…
